ከጥቂት ጊዜ በፊት በሬሆቮት ውስጥ በተከሰተ የዓመፅ ድርጊት ሁለት ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ልጆች ተወግተው መካከለኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሚገልጽ ሪፖርት ደርሷል – የሬሆቮት ጣቢያ የፖሊስ አባላት ወደ ስፍራው በመድረስ የድርጊቱን ሁኔታዎች በተመለከተ ምርመራ የጀመሩ ሲሆን በድርጊቱ የተጠረጠሩትን ለማግኘት አሰሳ እያደረጉ ነው። የድርጊቱ መነሻ ወንጀል ነክ ነው።