በአሪኤል በሚገኝ የግል የህፃናት ማቆያ ውስጥ የምትሰራ ሰራተኛ አቅመ ደካማ ላይ በደል ፈጽማለች በሚል ጥርጣሬ በሌሊት በቁጥጥር ስር ዋለች – የሰራተኛዋን ባህሪ በሚመለከት ጥርጣሬ ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ፣ በይሁዳ እና ሰማርያ (ሻይ) ዲስትሪክት የአሪኤል ጣቢያ ፖሊሶች በቅርቡ ምርመራ ከፍተዋል፤ በዚህም መሰረት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በህፃናት ማቆያው ውስጥ የተገጠሙ የደህንነት ካሜራዎች ተሰብስበዋል። ለጥርጣሬው ተጨባጭ ማስረጃ ከተገኘ በኋላ፣ ሰራተኛዋ በቁጥጥር ስር ውላ ለምርመራ ተላልፋለች።