በአሽኬሎን ውስጥ ከሚገኙ የግል መዋለ ህፃናት የተውጣጡ አንዲት የመዋለ ህፃናት አስተማሪ እና አራት ረዳቶች አቅመ ደካማ በሆኑ ለአካለ መጠን ባልደረሱ ህፃናት ላይ የጥቃት ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ጥርጣሬ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የአሽኬሎን ፖሊስ ጣቢያ በዚህ ሳምንት በደረሰው ሪፖርት መሰረት ምርመራ እያካሄደ ሲሆን፤ ከሪፖርቱም በከተማዋ ውስጥ በአንድ አስተዳደር ስር በሚንቀሳቀሱ ሁለት የግል መዋለ ህፃናት ውስጥ በታዳጊ ህፃናት ላይ የኃይል እርምጃ ተወስዷል የሚል ጥርጣሬ ተነስቷል።
ማስረጃዎችን እና ጥርጣሬውን የሚያጠናክሩ ተጨማሪ ግኝቶችን ማሰባሰብን ያካተቱ የምርመራ እርምጃዎች ከተከናወኑ በኋላ፤ በቀኑ ውስጥ የመዋለ ህፃናት አስተማሪዋ እና አራቱ ረዳቶች (የአሽኬሎን ነዋሪዎች) በሃላፊነት ባለው ሰው አቅመ ደካማ በሆነ ለአካለ መጠን ባልደረሰ ህፃን ላይ ጥቃት የመፈጸም ወንጀል ተጠርጥረው እንዲታሰሩ ተወስኗል።
በተጓዳኝም በቀጣዮቹ ቀናት መርማሪዎች አቤቱታቸውን ለመቀበል እና የክስተቱን ሁኔታዎች ማጣራት ለመቀጠል ሲባል፣ ጥቃት ደርሶባቸዋል ተብለው የተጠረጠሩትን የታዳጊ ህፃናት ወላጆችን ይጠራሉ።