በትሻ ቤአቭ ማታ የቤቱን ውድቀት እናስታውሳለን። በእኛ መካከል ያለውን የጥላቻ እና የ ማግለል አስከፊ ዋጋ እናስታውሳለን። ባለፉት ሦስት ዓመታት፣ በጋራ ጥረት፣ የሶስተኛውን ቤተ መቅደስ ውድቀት አምክነናል። የወንድማማቾች ጦርነት ፋንታ፣ ነፍሳችንን የሚሹትን ለመመከት ትከሻ ለትከሻ የሚዋጉ ወንድሞች ነበርን። ኃይላችንን አስተባበርን፣ እንደ አንበሳ ተዋጋን እናም አብረን የእስራኤልን ግዛት አዳንን። የእስራኤል ሕዝብ ደፋር ሕዝብ እንደሆነ፣ ደፋር ሠራዊት፣ የጀግኖች ትውልድ እንዳለው ለአለም አሳይተናል። የውድመትን ስጋት መከትን እና ታላላቅ ስኬቶችን አስመዝግበናል። ሥራው ገና ያላለቀ ቢሆንም፣ ብዙ ፈተናዎች ገና ከፊታችን ቢሉም፣ በእርግጠኝነት ልንወጣቸው እንደምንችል በነፍሴ ጥልቀት እርግጠኛ ነኝ። እንደ እስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር በእኛ መካከል ያለውን አንድነት ለማጠናከር አስባለሁ። ሰፊብሔራዊ መንግሥት፣ ደኅንነታችንን እና መጻኢ ዕጣ ፈንታችንን የሚጠብቅ የተረጋጋ መንግሥት ለመመስረት እሰራለሁ። በምርጫ ወቅት ይህንን እንዳይገባን የሚያደርጉ ክርክሮች እንደሚኖሩ አውቃለሁ፣ ነገር ግን ከሚመስለው በላይ እጅግ የተዋሃድን እንደሆንንም አውቃለሁ። እንዴት አውቃለሁ? ምክንያቱም በፈተና ሰዓት አግኝቻችኋለሁና። የጀግና ተዋጊዎቻችንን እገናኛለሁና። የእስራኤልን ህዝብ በሁሉም ክፍሎቹ በታላቅ ግርማው፣ እርስ በርሱ እጅ የሚዘረጋ ህዝብ አይቻለሁና። እና እነሆ ታላቁ ትምህርት፡ ባልተገባ ጥላቻ ወድመናል፣ በእስራኤል ፍቅር ተነስተናል። አብረን፣ በእግዚአብሔር እርዳታ፣ የእስራኤልን ዘላለማዊነት እናረጋግጣለን።