የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት (IDF) ቃል አቀባይ፦
የሜናሼ ብርጌድ ኃይሎች በሺን ቤት መመሪያ የሽብር ሴራዎችን ሲያራምዱ የነበሩ አራት አሸባሪዎችን በቁጥጥር ስር አዋሉ።
የዱቭደቫን ክፍል እና የፓራሹት ብርጌድ ተዋጊዎች በሺን ቤት መመሪያ ትናንት (ሐሙስ) በሜናሼ ብርጌድ አዛዥነት በጄኒን ከተማ አካባቢ የተካሄደ ዘመቻ አጠናቀዋል፤ በዘመቻውም የጦር መሣሪያ ሲነግዱ የነበሩ እና ቀደም ሲል በኦፕሬሽን ‹‹የብረት ግንብ›› በፈረሰው በጄኒን የሽብር ድርጅት ውስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩ አራት አሸባሪዎችን ይዘዋል።
አሸባሪዎቹ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ጸጥታ ኃይሎች ተላልፈዋል።