አሸባሪው አቡ እስማዒል በአሁኑ ወቅት የኻን ዩኒስ ብርጌድ አዛዥ ሙሐመድ ያዙሪ በሴፕቴምበር መጀመሪያ ላይ ከተገደለ በኋላ በይበልጥ የኻን ዩኒስ ብርጌድን በማስተዳደር እና በማዘዝ ረገድ ቁልፍ ሰው ሆኖ ያገለግላል።
በጋዛ ሰርጥ ውስጥ እንዳሉ ሌሎች ሆስፒታሎች ሁሉ በኻን ዩኒስ የሚገኘው የናስር ሆስፒታልም በሐማስ አገልግሎት ላይ ይውላል። ለምሳሌ በሆስፒታሉ ሁለተኛ ፎቅ ላይ ሲቪሎች እንዳይገቡበት በጥብቅ የሚጠበቅ እና ሙሐመድ አቡ እስማዒልን ጨምሮ የድርጅቱ አዛዦች ስለሚጠቀሙበት የሐማስ ወታደራዊ ዋና መሥሪያ ቤት ሆኖ ያገለግላል። በጦርነቱ በሙሉ በ«ናስር» ሆስፒታል በርካታ አስር ታጋቾች ተይዘው ቆይተዋል፤ አብዛኞቹ ከኪቡጽ ናሃል ኦዝ የተወሰዱ ሲሆኑ በውስጣቸውም ሴቶች፣ ልጆች፣ አረጋውያን እና የውጭ አገር ዜጎች ይገኙበታል።
እንዲሁም በጦርነቱ ወቅት በርካታ ታጋቾችን በምርኮ በማቆየት ረገድ ኃላፊነት ነበረበት፤ ከነዚህም መካከል የሚከተሉት ታጋቾች ይገኙበታል፦ ኒምሮድ ኮሄን፣ ማታን ጻንጋውከር፣ ኢዳን አሌክሳንደር፣ አቭራሃም መንጊስቱ፣ ኮሎኔል አሳፍ ሃማሚ (ነፍሳቸው በሰላም ትረፍ)፣ ሳጅን ሜጀር ኦዝ ዳንኤል እና ካፒቴን ኦመር ናውትራ (ነፍሳቸው በሰላም ትረፍ)።
በአቡ እስማዒል ላይ ከተፈጸመው ጥቃት ጎን ለጎን በሆስፒታሉ ሕንፃ ግቢ ውስጥ የነበሩ ሌሎች አሸባሪዎችም ተመተዋል፤ ከእነዚህም መካከል በውጊያ እና አስተዳደራዊ ድጋፍ ሰጪ ሻለቃ የምህንድስና ክፍል የቡድን መሪ የነበረው ሙአዋድ ታውፊቅ ማሕሙድ አቡ ዛሪፋ እና በሐማስ የስለላ ዋና መሥሪያ ቤት ኦፕሬሽን ክፍል የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ የነበረው ኻሌድ ኦሳማ አቡ አንዛ ይገኙበታል።
አሸባሪዎቹ የ«ናስር» ሆስፒታል ግቢን ዋና መሥሪያ ቤት ካደረጉ እና በጦርነቱ ወቅት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን የብርጌዱን ወታደራዊ አቅም እንደገና ለመገንባትና በኃይሎቻችን ላይ በርካታ የሽብር ጥቃቶችን ለማቀድ ከውስጡ ሆነው ሲንቀሳቀሱ ከቆዩ በኋላ ስጋቱን ለማስወገድ ከአየር ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።
ከጥቃቱ በፊት በሆስፒታሉ ሕንፃ እና እጃቸው በሌለበት ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በተቻለ መጠን ለመቀነስ የጥንቃቄ እርምጃዎች ተወስደዋል። በተጨማሪም ጥቃቱ የብርጌድ አዛዡ እና አሸባሪዎቹ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ያደርጉበት በነበረው ክፍል ላይ ብቻ ያነጣጠረ ነበር።
በተጨማሪም ጥቃቱ ከመፈጸሙ በፊት የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት (IDF) በሆስፒታሉ ውስጥ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዲቆም በተደጋጋሚ ጊዜያት፣ በቅርቡም ጭምር አስጠንቅቆና ጠይቆ ነበር። ማስጠንቀቂያዎቹ ቢሰጡም በሆስፒታሉ ውስጥ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ አልቆመም።