በላቪ ደን ውስጥ በተፈጸመ ግድያ ተሳትፈዋል የተባሉ ሦስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። ትናንት ከሰዓት በኋላ በጎላኒ መገናኛ አቅራቢያ በሚገኘው በላቪ ደን ውስጥ ህይወቱ ያለፈ ሰው መገኘቱን የሚገልጽ ሪፖርት ደረሰ። የሰሜን ዲስትሪክት ኃይሎች የክስተቱን ሁኔታ በተመለከተ ምርመራ የጀመሩ ሲሆን፣ በግድያው ስፍራ የተካሄደውን የሁኔታ ግምገማ ተከትሎ ምርመራው ለሰሜን ዲስትሪክት ማዕከላዊ ክፍል ተሰጥቷል። በዚህም መሃል የተገደለው ሰው ራቢ ኦበይዲያ (የይሁዳ እና ሰማርያ ነዋሪ፣ የ38 ዓመት) መሆኑ ታውቋል። በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ፣ በተከናወኑ የምርመራ ተግባራት ማዕቀፍ፣ በግድያው ተሳትፈዋል የተባሉ ሦስት ተጠርጣሪዎች (ሁለት ወንዶችና አንዲት ሴት፣ የቱርአን ነዋሪዎች) በቁጥጥር ስር ውለዋል።