በቀኑ ውስጥ የወይራ ለቀማ እንቅስቃሴ ካልተቀናጀበት እና የተዘጋ የወታደራዊ ቀጠና ትዕዛዝ ካለበት የእርሻ ቦታ በርካታ አክቲቪስቶች መኖራቸውን የሚገልጽ ሪፖርት ከእስራኤል መከላከያ ሠራዊት (IDF) ደርሷል። በተጨማሪም አክቲቪስቶቹ የወታደሮቹን መመሪያዎች ለመስማት፣ ማንነታቸውን ለእነሱ ለማሳወቅ እና ቦታውን ለቀው ለመውጣት ፈቃደኛ አልሆኑም።
ወደ ስፍራው የተጠሩት የኬብሮን ጣቢያ ፖሊስ አባላት 11 የውጭ ሀገር አክቲቪስቶችን እና አንድ ፍልስጤማዊን ተረክበው የተዘጋ የወታደራዊ ቀጠና ትዕዛዝን በመጣስ እና ወታደር ተግባሩን በሚያከናውንበት ወቅት እንቅፋት በመፍጠር ወንጀሎች ለምርመራ አስተላልፈዋቸዋል። በውጭ ሀገር አክቲቪስቶቹ ላይ በተደረገ ምርመራ ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ በእስራኤል ሀገር ላይ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች፣ ከሌሎችም መካከል ለአሸባሪዎች እና ለሽብር ድርጊቶች የውዳሴ እና የማሞገሻ ቃላትን በማሰራጨት፣ በእስራኤል ላይ በሚደረጉ የቦይኮት ድርጅቶች ውስጥ በመሳተፍ እና ለእንዲህ ዓይነቱ እንቅስቃሴ ገንዘብ በማሰባሰብ በንቃት የተሳተፉ መሆናቸው ተረጋግጧል።
ሁሉም የውጭ ሀገር ተጠርጣሪዎች በእስር ላይ የዋሉ ሲሆን ከእስራኤል ሀገር ስለመባረራቸው ለሚደረግ የዳኝነት ችሎት (hearing) ለሕዝብ እና የኢሚግሬሽን ባለሥልጣን ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።


