በኦር አኪቫ በተከሰተ እና ሁለት ወንዶች በጽኑ እና በመካከለኛ ደረጃ በቆሰሉበት የጩቤ ወጋት ክስተት ውስጥ እጃቸው አለበት የተባሉ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የሀደራ ጣቢያ የፖሊስ አባላት ክስተቱን ተከትሎ ምርመራ የጀመሩ ሲሆን ክስተቱ ከተፈጸመ ከ24 ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በኢየሩሳሌም የተገኙትን ተጠርጣሪዎች አድራሻ ፈልገው በመያዝ በቁጥጥር ስር ማዋል ችለዋል። ሁለቱ ተጠርጣሪዎች በሀደራ ጣቢያ ለሚደረገው ምርመራ ተላልፈዋል።