ባሳለፍነው አርብ በኦር የሁዳ ከአንድ የንግድ ተቋም አጠገብ የተሰቀለውን የእስራኤል ሰንደቅ ዓላማ አንድ ተጠርጣሪ በእሳት ሲያቃጥል የሚያሳይ ሪፖርት እና ቪዲዮ ደርሷል። ሪፖርቱ እንደደረሰም የመሱቢም ጣቢያ ፖሊሶች ተጠርጣሪውን ለመለየት እና ለመያዝ ሰፊ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

በእረፍት ላይ የነበረ የመሱቢም ጣቢያ የጥበቃ ፖሊስ አባል ትናንት ተጠርጣሪውን በኦር የሁዳ ተመልክቶ በቁጥጥር ስር አውሎታል። የጣቢያው ፖሊሶችም ወደ ስፍራው በመድረስ ዕድሜው በ40ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኘውን እና የኦር የሁዳ ነዋሪ የሆነውን ተጠርጣሪ ለምርመራ ወስደውታል። ዛሬ ተጠርጣሪው የእስር ጊዜውን ለማራዘም በሚደረግ ችሎት በተል አቪቭ የማጅስትሬት ፍርድ ቤት ይቀርባል።