የዲስትሪክቱ ፖሊስ አባላት ባደረጉት ፈጣን ዘመቻ፣ አንዲት ሴት በተገደለችበትና ሌሎች 3 ሰዎች መጠነኛ እና ቀላል ጉዳት በደረሰባቸው በካፍር ማንዳ መንደር በሚገኝ የንግድ ተቋም ላይ የተፈናጣሪ የእጅ ቦምብ በመወርወር የተጠረጠሩ 3 ሰዎች ከጥቂት ጊዜ በፊት በቁጥጥር ስር ውለዋል። የተጠረጠረው ተሽከርካሪ ተደብቆ ተገኝቷል።

በካፍር ማንዳ መንደር በሚገኝ የንግድ ተቋም ላይ የተፈናጣሪ የእጅ ቦምብ ስለመወርወሩና በወቅቱም በ50ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ አንዲት ሴት ስለመገደላቸው እንዲሁም ሌሎች 3 ሰዎች ቀላል እና መጠነኛ ጉዳት ስለደረሰባቸው ከቀረበው ሪፖርት በመቀጠል፣ ከጥቂት ጊዜ በፊት በሰሜን ዲስትሪክት ፖሊስ አባላት እና በድንበር ጥበቃ (ማጋቭ) ተዋጊዎች በተደረገ ሰፊ ዘመቻ፣ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም በክስተቱ እጃቸው እንዳለበት የተጠረጠሩ 3 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ወንጀሉ የተፈጸመበት ተሽከርካሪም ተደብቆ ተገኝቷል።

የፖሊስ ኮሚሽነር ራቭ ኒጻቭ ዳኒ ሌቪ እና የሰሜን ዲስትሪክት አዛዥ በቦታው የሚገኙ ሲሆን ስለ ክስተቱ ዝርዝር ሁኔታ፣ ስለ ምርመራው እንቅስቃሴ እና ስለተከናወኑት እስራቶች ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

የፖሊስ ኮሚሽነሩ በክስተቱ እጃቸው ያለበትን ሁሉ በቁጥጥር ስር ለማዋል እና ሁሉንም ኃይሎችና ግብአቶች ስራ ላይ ለማዋል የሚያስፈልጉ እርምጃዎች በሙሉ እንዲወሰዱ መመሪያ ሰጥተዋል።