በእስራኤል ፖሊስ የቴል አቪቭ አውራጃ ማዕከላዊ ክፍል ፖሊስ አባላት በኦር የሁዳ የዕጅ ቦንብ በመወወር አምስት ዜጎችን አቁስሎ ሲሸሽ የነበረ ተጠርጣሪ አዙ። በግንቦት 26 ቀን በኦር የሁዳ ኑቭ ራቢን ሰፈር ውስጥ በሚገኝ አንድ ቢዝነስ ላይ የዕጅ ቦንብ በመወወር ምክንያት የተለያየ የጉዳት መጠን የደረሰባቸው አምስት ዜጎች መኖራቸው ሪፖርት ደርሶ ነበር። የቴል አቪቭ ማዕከላዊ ክፍል ምርመራ በመላው ጉሽ ዳን ክልል ውስጥ በተፈጸሙ በርካታ የጥቃት እና የጦር መሣሪያ አጠቃቀም ወንጀሎች ሶስት ተከሳሾች ላይ ክስ እንዲመሰረት አድርጓል። የቡድኑ አካል የሆነ ሌላ ተጨማሪ ተጠርጣሪ (33) አምልጦ ለብዙ ወራት ሲሸሽ ቆይቷል። ባለፈው አርብ ዕለት ተጠርጣሪው ተይዞ ለምርመራ ተላልፏል።
የቴል አቪቭ አውራጃ ማዕከላዊ ክፍል ፖሊስ አባላት በኦር የሁዳ የዕጅ ቦንብ በመወወር አምስት ዜጎችን አቁስሎ ሲሸሽ የነበረ ተጠርጣሪ ያዙ
የእስራኤል ፖሊስ በኦር የሁዳ 5 ዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሰውን የዕጅ ቦንብ ጥቃት ፈጽሞ ሲሸሽ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር አዋለ።


