የፖሊስ ዋና አዛዥ (መፍካል) ራቭ ኒጻቭ ዳኒ ሌቪ ከሆፍ (የባህር ዳርቻ) አውራጃ አዛዥ ኒጻቭ ይሂኤል ቦሃዳና ጋር በመሆን የህዝብ ፀጥታን ለመጠበቅ እና የምርጫ ሂደቱን ደህንነት ለማስከበር የፖሊስ ዝግጅት አካል በሆነ መልኩ ዛሬ ጠዋት በአረብ ማህበረሰብ ውስጥ በጂስር አ-ዛርቃ እና በፉሬይዲስ ጉብኝት አድርገዋል።
በጉብኝቱ ወቅት ዋና አዛዡ እና የአውራጃው አዛዥ በመስክ ላይ ያለውን የኃይሎች ዝግጅት በቅርበት የተመለከቱ ሲሆን፥ ከፖሊስ አባላቱ ጋር ተነጋግረዋል፤ እንዲሁም የነዋሪዎችን ደህንነት ለማረጋገጥ እና ሁሉም ዜጎች ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው በሰላም፣ በነፃነት እና በአግባቡ ድምጽ እንዲሰጡ ለማስቻል ሙያዊ እና ቁርጠኛ የሆነ እንቅስቃሴ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።


