በአያሎን አውራጃ የያፋ ፖሊስ ጣቢያ ፖሊሶች ትናንት ምሽት በያፋ፣ የፈት ጎዳና ላይ በተከሰተና ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅን ጨምሮ 4 ሰዎች በቆሰሉበት በስለት የመወጋጋት ጥቃት የታጀበ የኃይል ድርጊት ውስጥ እጃቸው አለበት የተባሉ 3 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

ትናንት ምሽት በ22:30 በያፋ፣ የፈት ጎዳና ላይ ስለተከሰተና ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅን ጨምሮ 4 ሰዎች ስለቆሰሉበት የፀብ አደጋ ሪፖርት ደርሷል። ከተጎጂዎቹ መካከል 2ቱ ለህክምና እርዳታ ተወስደዋል።

ሪፖርቱ እንደደረሰ በአያሎን አውራጃ የያፋ ጣቢያ ፖሊሶች ስፍራው ደርሰው፣ የክስተቱን ሁኔታዎች አስመልክቶ ምርመራ የጀመሩ ሲሆን ማስረጃዎችን ማሰባሰብም ጀምረዋል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ፣ በኃይል ድርጊቱ ውስጥ እጃቸው አለበት የተባሉ 3 ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል። ተጠርጣሪዎቹ በያፋ ጣቢያ ለምርመራ የተላለፉ ሲሆን፣ በምርመራው ማጠቃለያ ላይም ታስረዋል።