የይሁዳ እና ሰማርያ ዲስትሪክት የፖሊስ አባላት በማህበራዊ ሚዲያ በተሰራጨ ምስል ሳቢያ በኢያሪኮ አካባቢ በአንዲት ጋዜጠኛ ላይ የተፈጸመን የተጠረጠረ ጥቃት ማጣራት ጀመሩ።
ዛሬ ቀደም ብሎ፣ ከአንድ ሳምንት ገደማ በፊት በኢያሪኮ ከተማ አካባቢ በአንዲት የውጭ አገር ጋዜጠኛ ላይ የተፈጸመን ጥቃት ያሳያል የተባለ እና በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ ተንቀሳቃሽ ምስል ለፖሊስ ደርሷል።
ተንቀሳቃሽ ምስሉ እንደደረሰ በበቅዓ ጣቢያ ምርመራ የተከፈተ ሲሆን፤ በእውነቱ ላይ ለመድረስ ተጠርጣሪዎችን ለማግኘት ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን ከጋዜጠኛዋ ጋር ግንኙነት ማድረግን እና ከእርሷ ቃል መቀበልን ጨምሮ አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎች ሁሉ እየተወሰዱ ነው።

