የ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከላት (CDC) አዲስ መሪዎችን በማስታወቄ ደስተኛ ነኝ። በሚያስደንቅ ሁኔታ ችሎታ ያላቸውን ዶ/ር ኤሪካ ሽዋርትዝ፣ ኤምዲ፣ ጄዲ፣ ኤምፒኤች፣ የ CDC ዳይሬክተር አድርጎ መሾም ትልቅ ክብር ነው። ኤሪካ ከ ብራውን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ እና የ ሕክምና ትምህርት ቤት የተመረቁ ሲሆን፣ በዓለም ላይ ታላቁ እና ኃያሉ ኃይል በሆነው በ አሜሪካ ወታደራዊ ኃይል ውስጥ የ ሕክምና ሐኪም በመሆን የተከበረ አገልግሎት ሰጥተዋል፣ ከዚያም በመጀመሪያ የስልጣን ዘመኔ ምክትል ቀዶ ጥገና ሐኪም በመሆን አገልግለዋል። እርሳቸው ኮከብ (STAR) ናቸው! ሴን ስሎቨንስኪ የ CDC ምክትል ዳይሬክተር እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ፣ ዶ/ር ጄኒፈር ሹፎርድ፣ ኤምዲ፣ ኤምፒኤች የ CDC ምክትል ዳይሬክተር እና ዋና የ ሕክምና ኦፊሰር፣ እንዲሁም ዶ/ር ሳራ ብሬነር፣ ኤምዲ፣ ኤምፒኤች ለ የሕዝብ ጤና ከፍተኛ አማካሪ ሆኖ ለ ዋና ፀሐፊ ሮበርት ኤፍ. ኬኔዲ ጁኒየር መሾሙን ስገልጽ በደስታ ነው። እነዚህ ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸው የ ሕክምና ሐኪሞች በ እንቅልፍኛ ጆ ስር በ “ትእዛዞች” ላይ ብቻ ያተኮረ ፍጹም አደጋ በሆነው በ CDC ውስጥ የሳይንስ ወርቃማ ደረጃን ለመመለስ እውቀት፣ ልምድ እና ከፍተኛ ዲግሪዎች አሏቸው። አሜሪካን እንደገና ጤናማ እና ታላቅ ማድረግ ስንቀጥል CDCን በመምራት ግሩም ሥራ ይሠራሉ! ፕሬዚዳንት ዶናልድ ጄ. ትራምፕ

Credits from Donald Trump Truth Social Network