የእስራኤል መከላከያ ሠራዊትቃል አቀባይ፡ ሥጋትን ለማስወገድ፡ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በጥቅምት 7 እልቂት ወደ አገር ውስጥ ሠርጎ ገብቶ የሳጅን ሻክድ ዳሃን ዘኲ መታሰቢያቸው ይኑር አስከሬን በመጥለፍ ውስጥ የተሳተፈ አሸባሪ አስወገደ። የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በጋዛ ሰርጥ በካን ዩኒስ አካባቢ ቀደም ሲል በዚህ ሳምንት ሰኞ ዕለት ጥቃት ፈጽሞ፥ የሐማስ ሽብር ድርጅት ወታደራዊ ክንፍ አዛዥ የሆነውን ኢብራሂም አላም አስወግዷል። አሸባሪው በጥቅምት 7 እልቂት ወደ እስራኤል መንግሥት ግዛት ሠርጎ በመግባት በርካታ የእስራኤል ዜጎች በመገደል ሂደት ውስጥ የተሳተፈ ሲሆን፥ የሳጅን ሻክድ ዳሃን ዘኲ መታሰቢያቸው ይኑር አስከሬን ወደ ሐማስ ምርኮ በመጥለፍ ሂደት ውስጥም ተሳትፏል። በቀድሞው ዕለት ማክሰኞ በሌላ ጥቃት የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት የሐማስ ሽብር ድርጅት ወታደራዊ ክንፍ አሸባሪ የሆነውን ሙዕተሲም ሙሐመድ ሱለይማን ሳላህ ላይ ጥቃት ፈጽሞ አስወግዶታል። በቅርብ ጊዜ ውስጥ አሸባሪዎቹ በእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች እና በእስራኤል መንግሥት ዜጎች ላይ የሽብር ዕቅዶችን ሲያራመዱ የነበረ ሲሆን፥ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ስልታዊ በሆነ መንገድ በመጣስ የሐማስ ሽብር ድርጅትን አቅሞች ለማቋቋም ሠርተዋል። አሸባሪዎቹ የነበሩባቸውን ሥጋት ለማስወገድ ሲባል ከሰማይ ተወግደዋል። ከጥቃቶቹ በፊት በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ትክክለኛ መሣሪያዎችን መጠቀምን እና የአየር ላይ ክትትሎችን ጨምሮ እርምጃዎች ተወስደዋል። በደቡባዊ ዕዝ ትዕዛዝ ሥር ያሉ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች ከስምምነቱ ጋር በሚስማማ መልኩ በአካባቢው ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን ማንኛውንም ቀጥተኛ ሥጋት ለማስወገድ መስራታቸውን ይቀጥላሉ።
ሥጋትን ለማስወገድ፡ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በጥቅምት 7 እልቂት ወደ አገር ውስጥ ሠርጎ ገብቶ የሳጅን ሻክድ ዳሃን አስከሬን በመጥለፍ ሂደት ውስጥ የተሳተፈ አሸባሪ አስወገደ
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በካን ዩኒስ ባካሄደው ኦፕሬሽን በጥቅምት 7 እልቂት እና የሳጅን ሻክድ ዳሃን አስከሬን በመጥለፍ ሂደት ውስጥ የተሳተፈ አሸባሪ አስወገደ።



