የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት (IDF) ቃል አቀባይ፦ በምናሼ ብርጌድ በተካሄደ ልዩ ዘመቻ፦ የዱቭዴቫን ክፍለ ጦር ተዋጊዎች በሺን ቤት መሪነት ከተበተነው በጄኒን የነበረ የሽብር ድርጅት አሸባሪን በቁጥጥር ስር አዋሉ።

የዱቭዴቫን ክፍለ ጦር ተዋጊዎች ዛሬ ጠዋት (ሐሙስ) በምናሼ ብርጌድ ስር በምትገኘው በጄኒን ከተማ ልዩ ዘመቻ አጠናቀዋል፤ በእዚህም ማዕቀፍ ውስጥ ኃይሎቹ በሺን ቤት መሪነት፣ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች በሰሜን ሰማርያ ካምፖች ውስጥ የሽብር ድርጅቶችን ለማክሸፍ በንቅናቄ በሠሩበት “የብረት ግንብ” ዘመቻ ወቅት ከተበተነው በጄኒን የነበረ የሽብር ድርጅት አባል የነበረ አሸባሪን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

አሸባሪው እንደ ዋና የጦር መሣሪያ ነጋዴ ሆኖ ያገለገለ ሲሆን ለሽብር ድርጅቱ መሣሪያዎችን በመግዛት እና በማስተላለፍ ረገድ ተንቀሳቅሷል።

የፀጥታ ኃይሎች በይሁዳ እና ሰማርያ ዲቪዥን ውስጥ ሽብርተኝነትን ለማክሸፍ እና የእስራኤል አገር ዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ በቅድመ-ተነሳሽነት እና በማጥቃት እርምጃ መሥራታቸውን ይቀጥላሉ።