በ36ኛ ዲቪዥን ዕዝ ሥር የሚገኙት የ188ኛ ብርጌድ የውጊያ ቡድን ኃይሎች፣ በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ለአንድ ዓመት ከስምንት ወራት ያህል ከቆዩና የስልጠና ጊዜ ካጠናቀቁ በኋላ፣ በእስራኤል ሀገር ላይ የተደቀኑ ሥጋቶችን ለማስወገድ በቦፎርት ሪጅ እና ሊታኒ ወንዝ አካባቢ እየተንቀሳቀሱ ነው።
ኃይሎቹ ባከናወኑት እንቅስቃሴ ወቅት ከ340 በላይ የጦር መሣሪያዎችን ያገኙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል፡ የ’RPG’ ሮኬቶች፣ ፀረ-ታንክ ሚሳኤሎች፣ የሞርታር ጥይቶች፣ ቀላል የጦር መሣሪያዎች፣ ፈንጂዎች፣ የእጅ ቦምቦች እና ጥይቶች ይገኙበታል።



በተጨማሪም በአንድ ንጹሐን መኖሪያ ቤት ውስጥ ወደ ሰባት ሜትር ያህል ጥልቀት ያለው ከመሬት በታች የተቆፈረ የመሿለኪያ መግቢያ ጉድጓድ የተገኘ ሲሆን በውስጡም የሕክምና እና የመኖሪያ ቁሳቁሶች ተገኝተዋል።



