የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ቃል አቀባይ፡- የሠራዊቱ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ኤያል ዘሚር ብርጋዴር ጄኔራል ተል ፖሊቲስን በዋሽንግተን የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ወታደራዊ ተወካይ አድርጎ ሾመ። መኮንኑ ወደ ሜጀር ጄኔራል ማዕረግ ከፍ ይላሉ። በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ከጥቂት ወራት በፊት በተደረገው የስራ ምደባ ውይይት ስምምነት መሠረት ብርጋዴር ጄኔራል ባርክ ሂራም የክዋኔዎች (ኦፕሬሽን) ክፍል ኃላፊ ሆኖ የሚሾም ሲሆን በመጪዎቹ ቀናትም ስራውን ይረከባል። ዋና አዛዡ መኮንኖቹን በስልክ አነጋግሮ እንኳን ደስ አላችሁ አላቸው።ሹመቶቹም በወከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ጸድቀዋል።