የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት እና የሻባክ ቃል አቀባዮች የጉባኤ መግለጫ፡ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት እና ሻባክ ትላንት እሁድ በሰሜን የጋዛ ሰርጥ ባደረጉት ጥቃት በጥቅምት 7 እለት ወደ እስራኤል ግዛት ሾልኮ ገብቶ በነበረው የእስላማዊ ጂሃድ (ጋእፕ) የጸረ-ሰላም ድርጅት አባል በሆነው በዘሀር በርሀም ኸሊል አቡ ሳሌም ላይ እርምጃ ወስደው አስወገዱት። አቡ ሳሌም እስራኤላውያን ዜጎችን ከቤታቸው አግቶ በመውሰድ እና በማንገላታት ላይ ተሳትፏል። በተጨማሪም በጦርነቱ ወቅትም ሆነ በቅርብ ጊዜያት አቡ ሳሌም በእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች እና በእስራኤል ግዛት ዜጎች ላይ በርካታ የጸረ-ሰላም እቅዶችን ለማራመድ ሞክሯል። አቡ ሳሌም በጋዛ ሰርጥ እየተንቀሳቀሱ ለሚገኙት ኃይሎቻችን ስጋትደቅኖ የነበረ ሲሆን በአየር ላይ ጥቃት ተወግዷል። የደቡብ ዕዝ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች ከስምምነቱ ጋር በሚስማማ መልኩ በግዛቱ ውስጥ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን ማንኛውንም ስጋት ለማስወገድ እርምጃቸውን ይቀጥላሉ።
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት እና የሻባክ ቃል አቀባዮች የጉባኤ መግለጫ፡ መከላከያ ሠራዊት እና ሻባክ በጥቅምት 7 ወደ እስራኤል ሾልኮ በመግባት ዜጎችን በዕገታ በመውሰድ የተሳተፈ የእስላማዊ ጂሃድ (ጋእፕ) የጸረ-ሰላም ድርጅት አባላ የሆነ አሸባሪ አስወገዱ
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት እና ሻባክ በጥቅምት 7 ወደ እስራኤል ሾልኮ በመግባት ዜጎችን አግቶ የወሰደውን የእስላማዊ ጂሃድ (ጋእፕ) አሸባሪ ዘሀር በርሀም ኸሊል አቡ ሳሌምን አስወገዱ።
ፎቶ በየእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 29 ቀን 2026
አገልግሎቶች
ርዕሰ ጉዳዮች