የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች ትላንት አርብ ከሰማርያ እግረኛ ብርጌድ ስር ከምትገኘው ከቡርቃ መንደር አጠገብ ባለው አካባቢ እሳት መነሳቱ ከቀረበ ሪፖርት ጋር ተያይዞ ወደ ስፍራው ተንቀሳቅሰዋል፤ ምንም ዓይነት ጉዳት አልደረሰም። ሲደርሱም ኃይሎቹ በአካባቢው ተጠርጣሪዎችን ፍለጋ አድርገዋል እና ከጥቂት ጊዜ በኋላ እሳቱን ማቀጣጠላቸውን ያመኑ ሁለት አሸባሪዎችን በቁጥጥር ስር አውለዋል አሸባሪዎቹ ለተጨማሪ ምርመራ ለጸጥታ ኃይሎች ተላልፈው ተሰጥተዋል። የጸጥታ ኃይሎች በይሁዳ እና ሰማርያ ሐገረ ገዢ (ክፍለ ጦር) ዙሪያ ሽብርተኝነትን ለማክሸፍ እና የእስራኤል ግዛት ዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ በንቃት እና በማጥቃት እርምጃቸውን ይቀጥላሉ።