የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት እና ሺን ቤቴ ትናንት (ሐሙስ) በጋዛ ሰርጥ ውስጥ በሚገኙ በርካታ አካባቢዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ጥቃት ፈጽመዋል፣ ከአየርም ላይ አራት የሐማስ እና የጋአፕ (የፍልስጤም እስላማዊ ጂሃድ) የጦር መሣሪያ ማከማቻዎችን አወድመዋል። 

 

በማከማቻዎቹ ውስጥ ሮኬቶችን፣ መሣሪያዎችን (ፈንጂዎችን)፣ አሸንዳዎችን (ሞርታሮችን)፣ ‘ክላሽኒኮቭ’ የተባሉ ጠመንጃዎችን እና ተጨማሪ የውጊያ ዕቃዎችን ጨምሮ የተለያዩ ዓይነት አሥርዮሽ (ደርዘን) የሚቆጠሩ የጦር መሣሪያዎች ተከማችተው ነበር። 

የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት እና ሺን ቤቴ በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ያሉትን አቅሞች ለማዳከም እና እንደገና ለማቋቋም የሚደረግን ማንኛውንም ሙከራ ወይም ኃይሎቻችንን ለመጉዳት ሲባል የጦር መሣሪያዎችን ይዞ ለመቆየት የሚደረግን ጥረት ለማክሸፍ በቁርጠኝነት መስራታቸውን ይቀጥላሉ።

ከጥቃቶቹ በፊት በህዝቡ ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ ሲባል ለሕዝብ ቀደምት ማስጠንቀቂያዎች ተሰጥተዋል፤ይህም ትክክለኛ ጥይቶችን እና የአየር ላይ ክትትልን ከመጠቀም ጋር ተያይዞ የተከናወነ ነው።

የደቡብ ዕዝ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች ከስምምነቱ ጋር በተጣጣመ መልኩ በአካባቢው ተሰማርተዋል እንዲሁም ማንኛውንም አስቸኳይ አደጋ ለማስወገድ መስራታቸውን ይቀጥላሉ።