የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት (IDF) ቃል አቀባይ፦

የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ከሐማስ የሽብር ድርጅት 3 የኑኽባ አሸባሪዎችን ገድሏል፦ ከመካከላቸው አንዱ አሸባሪ ወደ ኪቡትዝ ኒር ኦዝ በመዝለቅ በጥቅምት 7 እልቂት ወቅት የእስራኤላውያን ሲቪሎችን በማገት ተሳትፏል።

የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ባለፈው ሳምንት (ሐሙስ) በደቡብ የጋዛ ሰርጥ ጥቃት የፈጸመ ሲሆን፣ በሐማስ የሽብር ድርጅት ወታደራዊ ክንፍ ውስጥ የኑኽባ አሸባሪ የነበረውን አህመድ ሙሐመድ አህመድ ባራካን ገድሏል።

አሸባሪው በጥቅምት 7 እልቂት ወቅት ከኪቡትዝ ኒር ኦዝ የተወሰዱትን አሌክሳንደር ዳንሲግን (ነፍሳቸውን ይማረውና) ጨምሮ በርካታ እስራኤላውያን ሲቪሎችን በማገቱ ሂደት ተሳትፏል።

በተጨማሪም በጦርነቱ ወቅት በደቡብ የጋዛ ሰርጥ አካባቢ ኒምሮድ ኮሄንን ጨምሮ በርካታ ታጋቾችን ይዞ በማቆየት ረድቷል።

በሳምንቱ መጨረሻ (ዓርብ) በሰሜን የጋዛ ሰርጥ በተፈጸመ ጥቃት፣ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ከሐማስ ወታደራዊ ክንፍ ተጨማሪ 2 አሸባሪዎችን ገድሏል፦ እነሱም የኑኽባ ክፍል አዛዥ የሆነው ኦማር አዋዳልላህ እና የኑኽባ አሸባሪ የሆነው ሙዕታዝ ማሕሙድ ሙሐመድ አል-ናማር ናቸው።

በጦርነቱ ሁሉ እና በተለይም በቅርቡ አሸባሪዎቹ በእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች እና በእስራኤል መንግሥት ዜጎች ላይ የሽብር ሴራዎችን ሲያራምዱ፣ እንዲሁም የተኩስ አቁም ስምምነቱን በስልታዊ መንገድ እየጣሱ የሐማስ የሽብር ድርጅት አቅሞችን መልሶ ለመገንባት ሲሰሩ ቆይተዋል። አሸባሪዎቹ ያስከተሉትን ሥጋት ለማስወገድ ከአየር ላይ ተገድለዋል።

በደቡባዊ ዕዝ ስር የሚገኙት የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች በስምምነቱ መሠረት በአካባቢው ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን፣ ማንኛውንም ሥጋት ለማስወገድ እርምጃ መውሰዳቸውን ይቀጥላሉ።