የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ቃል አቀባይ፦
በ7 ኦክቶበር እልቂት ወደ ሱፋ ጦር ሰፈር የወረረ የኑኽባ አዛዥ እና ወደ እስራኤል ግዛት የወረረ የፕላቶን አዛዥ፦ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት (IDF) በጋዛ ሰርጥ ከአሸባሪው ድርጅት ሐማስ ሦስት አዛዦችን ገደለ።
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በጋዛ ሰርጥ ጥቃት በማድረስ ከአሸባሪው ድርጅት ሐማስ ወታደራዊ ክንፍ በርካታ አሸባሪዎችን ገድሏል።
* በዚህ ሳምንት መጀመሪያ (እሑድ)፣ በ7 ኦክቶበር እልቂት ወደ ሱፋ ጦር ሰፈር የወረረው የኑኽባ አዛዥ አሸባሪው አነስ አክራም ሙሐመድ ሐማይዳ በኻን ዩኒስ አካባቢ ተገደለ።
* በዚህ ሳምንት መጀመሪያ (እሑድ)፣ በ7 ኦክቶበር እልቂት ወደ እስራኤል መንግሥት ግዛት የወረረው የምሥራቅ ጃባሊያ ሻለቃ የፕላቶን አዛዥ አሸባሪው አሽራፍ ማሕሙድ ዩሱፍ ዳሕላን በጋዛ ከተማ አካባቢ ተገደለ።
* ከትናንት በስቲያ (ሰኞ)፣ የምዕራብ ጃባሊያ ሻለቃ የኑኽባ አዛዥ አሸባሪው ማሕሙድ ዑስማን አብደላህ አልዋን በጋዛ ከተማ አካባቢ ተገደለ።
በጦርነቱ በሙሉ እና በተለይም በቅርቡ አሸባሪዎቹ በእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች እና በእስራኤል መንግሥት ዜጎች ላይ የሽብር ዕቅዶችን ሲያራምዱ የነበረ ሲሆን የተኩስ አቁሙን ስልታዊ በሆነ መንገድ በመጣስ የአሸባሪው ድርጅት ሐማስን አቅም መልሶ ለማቋቋም ሠርተዋል። አሸባሪዎቹ የተደቀነውን አደጋ ለማስወገድ በአየር ተገድለዋል።
በደቡብ ዕዝ ሥር ያሉ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች በስምምነቱ መሠረት በአካባቢው የተሰማሩ ሲሆን ማንኛውንም አደጋ ለማስወገድ እርምጃ መውሰዳቸውን ይቀጥላሉ።