የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ቃል አቀባይ፦
የሽብር ዕቅዶችን ለማራመድ በሚገናኙበት ወቅት፦ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በማዕከላዊ የጋዛ ሰርጥ በርካታ የሐማስ አሸባሪዎችን አጠቃ
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት (IDF) ከጥቂት ጊዜ በፊት ከሐማስ የሽብር ድርጅት ወታደራዊ ክንፍ የተውጣጡ በርካታ አሸባሪዎችን፣ በእስራኤል ዜጎች እና በእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች ላይ በማዕከላዊ የጋዛ ሰርጥ የሽብር ዕቅዶችን ለማራመድ በሚገናኙበት ወቅት አጥቅቷል።
ጥቃት ከተፈጸመባቸው አሸባሪዎች መካከል የኑክባ አሸባሪዎች እና በጥቅምት 7 እልቂት ወደ እስራኤል ግዛት ሰርገው የገቡ አሸባሪዎች ይገኙበታል።
በጦርነቱ በሙሉ እና በተለይም በቅርብ ጊዜያት፣ አሸባሪዎቹ የተኩስ አቁሙን ስልታዊ በሆነ መንገድ በመጣስ በእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች እና በእስራኤል ዜጎች ላይ የሽብር ዕቅዶችን ሲያራምዱ እንዲሁም የሐማስን የሽብር ድርጅት አቅም መልሶ ለመገንባት ሲሰሩ ቆይተዋል። አሸባሪዎቹ ያደቀኑትን ስጋት ለማስወገድ ከአየር ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት የጥቃቱን ውጤት አስመልክቶ ወደፊት ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል።



