የኮንግረስ አባል አሽሊ «ሂንሰን» በ2016፣ በ2020 እና በ2024 ባሸነፍኩባቸው እና በምወዳቸው አዮዋ ግዛት ለዩናይትድ ስቴትስ ሴኔት እየተወዳደረች ነው:: አሽሊን በደንብ አውቃታለሁ፣ እርሷም አሸናፊ ናት! አፍቃሪ ሚስት እና የሁለት ወንዶች ልጆች ኩሩ እናት የሆነችው አሽሊ አስደናቂ ሰው ናት፣ ለአዮዋ ሁልጊዜ አድርጋለች፣ በዩናይትድ ስቴትስ ሴኔትም ይህንን መቀጠል ትችላለች። ሥራዎችን ለመፍጠር፣ ግብር ለመቀነስ፣ በአስደናቂዎቹ የአዮዋ ሠራተኞቻችን በአሜሪካ የተሠሩ ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ፣ ታላላቆቹን አርሶ አደሮቻችንን እና የአሜሪካን ግብርና ለመደገፍ፣ ፈጠራን ለመደገፍ፣ ድንበራችንን ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ፣ ስደተኛ ወንጀለኞችን፣ ነፍሰ ገዳዮችን እና ሌሎች ወንጀለኞች ሀገራችንን በሕገ ወጥ መንገድ እንዳይገቡ ለማስቆም፣ ሠራዊታችንን/የጦር አርበኞቻችንን ለማጠናከር እና ሁልጊዜም ጥቃት ላይ የሚገኘውን ሁለተኛው ማሻሻያ ለመከላከል ጠንክራ እየሠራች ነው። አሽሊ «ሂንሰን» ግሩም ሴናተር ትሆናለች፣ ሙሉ እና አጠቃላይ ድጋፌም አላት። የምርጫ ቀን ማክሰኞ ሰኔ 2 ነው። ውጡና ለአሽሊ ድምፅ ስጡ — እሷ ፈጽሞ አታሳፍራችሁም! የመምረጫ አካባቢዎን እዚህ ይፈልጉ:

ክሬዲት ከዶናልድ ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል ኔትወርክ