የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ቃል አቀባይ፦

ስጋትን ለማስወገድ፦ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት በኦክቶበር 7 እልቂት ወደ ሬኢም ካምፕ የወረረውን የኑኽባ ቡድን መሪ ገደለ።

የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ከትናንት በስቲያ (ረቡዕ) በደቡብ የጋዛ ሰርጥ ጥቃት ፈጽሞ የሐማስ አሸባሪ ድርጅት ወታደራዊ ክንፍ የኑኽባ ቡድን መሪ የሆነውን አሸባሪውን ማኸር ዋሊድ አምር አል-ሐሲኒን ገድሏል። አሸባሪው በኦክቶበር 7 እልቂት ወቅት ወደ ሬኢም ካምፕ ወርሮ ገብቶ ነበር።

በቅርቡ አሸባሪው በእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች እና በእስራኤል ዜጎች ላይ የሽብር ዕቅዶችን ሲያራምድ እንዲሁም የተኩስ አቁሙን ስልታዊ በሆነ መንገድ በመጣስ የሐማስ አሸባሪ ድርጅትን ወታደራዊ አቅም እንደገና ለመገንባት ሲሠራ ቆይቷል። ስጋቱን ለማስወገድ አሸባሪው በአየር ላይ ጥቃት ተገድሏል።

በደቡብ ዕዝ ሥር ያሉ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች በስምምነቱ መሠረት በአካባቢው የተሰማሩ ሲሆን ማንኛውንም አፋጣኝ ስጋት ለማስወገድ እርምጃ መውሰዳቸውን ይቀጥላሉ።