ከ01-12/11 ባሉት ቀናት ውስጥ የጦር መሣሪያዎችን እና ወታደራዊ ቁሳቁሶችን የማስመለስ ዘመቻ ይካሄዳል። በቴክኖሎጂ እና ሎጂስቲክስ መምሪያ ዘመቻ ማዕቀፍ ውስጥ፣ በመደበኛ ወይም በተጠባባቂ አገልግሎት ላይ ባሉ ወታደሮች በአገልግሎታቸው ወቅት ከእስራኤል መከላከያ ሠራዊት (IDF) የተወሰዱ የጦር መሣሪያዎችን እና ወታደራዊ ቁሳቁሶችን ማንነትን የመግለጽ ግዴታ ሳይኖርባቸው እንዲሁም ዕቃውን ያለአግባብ በማውጣት፣ በመያዝ ወይም በመሸከም ክስ ሳይመሰረትባቸው መመለስ ይቻላል።

የዘመቻው ዓላማ ወታደራዊ ቁሳቁሶች በተዘጋጁ ጣቢያዎች እንዲረከቡና ወደ እስራኤል መከላከያ ሠራዊት (IDF) ይዞታ እንዲመለሱ በማድረግ የተደራጀ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ቁጥጥር የሚደረግበት አወሳሰድ እንዲኖር ማስቻል ነው። የመመለሻ ጣቢያዎች የመጠባበቂያ ኃይል አባላት በእጃቸው የሚገኘውን ቁሳቁስ በቀላሉ እና በተመቻቸ ሁኔታ መመለስ እንዲችሉ በመላ አገሪቱ በሚገኙ ወታደራዊ ሰፈሮችና ተቋማት ውስጥ ይቋቋማሉ። የመመለሻ ጣቢያዎቹ ከእሑድ እስከ ሐሙስ ከጠዋቱ 08:00 እስከ ማታው 20:00 ክፍት ይሆናሉ።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር *6008 ወደ መረጃ ማዕከሉ መደወል ይቻላል።
የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት (IDF) በእጁ ትጥቅ ወይም ወታደራዊ ቁሳቁስ ያለውን ማንኛውንም ሰው ዕድሉን ተጠቅሞ እንዲመልስ ጥሪ ያቀርባል። ቁሳቁሶቹን መመለስ የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ እና ፀጥታን ለማጠናከር ይረዳል።
የመመለሻ ጣቢያዎች ዝርዝር፦
የደቡብ ቀጣና፦
- ማሓኔ ሬዒም
- የደቡብ ዕዝ መግቢያ በር (ቤር ሼቫ)
- የክፍለ ጦር 252 መግቢያ በር (ኦሃሊም)
- የስዴ ቴይማን መግቢያ በር
- የናሓል ሶሬክ መግቢያ በር
- የቅፂዖት መግቢያ በር
- ፕሉጎት
- የአካባቢ ክፍለ ጦር 80
- ማሓኔ ኡሪም
- ቂርያት ሃሃድራኻ (የስልጠና ካምፓስ)
- ማሓኔ ናታን
- ሚሽማር ሃኔጌቭ የጦር ሰፈር
- ሓፆር
- ሓፀሪም
- ፓልማሒም
- የቀይ ባሕር አውድ – ኤላት
- የሚትካን አዳም መግቢያ በር
- የማሓኔ አማኑኤል መግቢያ በር – ጁሊስ
- የማሓኔ ላስኮቭ መግቢያ በር – ባሃድ 1
- ባሃላትዝ 14 ፁቄይ ዖቭዳ
- ማሓኔ ፁር
- ማሓኔ ሺቅሚም አስቀላን
የሰሜን ቀጣና፦
- ማሓኔ ናፋሕ
- ማሓኔ ሺምሾን – ጎላኒ መጋጠሚያ
- ማሓኔ ቲራ
- ማሓኔ ማጋል 80
- ሆስፒታል 10
- ማሓኔ ታቮር
- ማሓኔ አሚዓድ
- ማሓኔ ሓቫት ሃሾሜር
- ማሓኔ ፂፖሪት
- ማሓኔ ሚስጋቭ
- ማሓኔ ኤልያቂም
- ማሓኔ ፊሎን
- ማሓኔ ሽራጋ
- ማሓኔ ናዝሬት
- ማሓኔ ሃሖትሪም
- ማሕቬህ አሎን
- ራማት ዳቪድ
የማዕከል ቀጣና፦
- ቢንያሚን የአካባቢ ብርጌድ
- ማሓኔ ቤን አሚ – ቤት ነባላ
- ኤትስዮን የአካባቢ ብርጌድ
- ምናሼ የአካባቢ ብርጌድ
- ኤፍሬም የአካባቢ ብርጌድ
- ሚክሎል ኦፈር
- ማሓኔ ሊፕኪን
- ማሓኔ ሾምሪያ
- ማሓኔ ናሕሾኒም
- የአካባቢ ብርጌድ 417
- ማሓኔ ነሔምያ
- ባአፕ ላኺሽ
- አናቶት
- ማሓኔ ረሓቭዓም
- ማሓኔ ኤሬዝ
- ማሓኔ ኦፍሪት
- ማሓኔ ጊድዖኒም
- ፀሪፊን – የኢየሩሳሌም በር
- ማሓኔ ማክሌፍ (የሰው ኃይል መምሪያ)
- ቴል ሃሾሜር – የደቡብ በር
- ግሊሎት – የሲቪል ጣቢያ
- የሚትካን አዳም መግቢያ በር
- ሃቂርያ የጦር ሰፈር
- ቤት ሊድ
ጥያቄዎችና መልሶች፡ ስለ ትጥቅ እና ቁሳቁስ መመለስ ዘመቻ ማወቅ ያለብዎት ነገር ሁሉ
በዘመቻው ቅድመ ሁኔታዎች እና መመሪያዎች መሠረት ዕቃዎቹን ያለአግባብ በማውጣት፣ በመያዝ ወይም በመሸከም ክስ ሳይመሰረትባቸው መመለስ ይቻላል።
አይደለም። በዘመቻው ማዕቀፍ ውስጥ ዕቃዎችን ማንነትን የመግለጽ ግዴታ ሳይኖር መመለስ ይቻላል።
በአገልግሎት ወቅት ከእስራኤል መከላከያ ሠራዊት (IDF) የተወሰዱ ማናቸውንም የጦር መሣሪያዎችን (ትጥቅ) እና ወታደራዊ ቁሳቁሶችን መመለስ ይቻላል። ስለ አንድ የተወሰነ ዕቃ ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ዘመቻው የመረጃ ማዕከል መደወል ይቻላል።
በአገልግሎታቸው ወቅት ከእስራኤል መከላከያ ሠራዊት (IDF) የተወሰዱ ትጥቅ ወይም ወታደራዊ ቁሳቁሶች በእጃቸው የሚገኙ በመደበኛ ወይም በተጠባባቂ አገልግሎት ላይ ያሉ ወንዶችና ሴቶች ወታደሮች።
የተዘጋጁ የመመለሻ ጣቢያዎች በመላ አገሪቱ በሚገኙ የጦር ሰፈሮች ውስጥ ይቀመጣሉ። ተስማሚውን ጣቢያ ከሙሉ የአድራሻዎች ዝርዝር ወይም በስልክ ቁጥር *6008 በመረጃ ማዕከሉ በኩል ማግኘት ይቻላል።
አይደለም። መመለስ የሚከናወነው በመላ አገሪቱ በሚገኙ የጦር ሰፈሮች ውስጥ በሚቋቋሙ የተለዩ ጣቢያዎች ነው።
ተስማሚውን ጣቢያ ለማግኘት የጣቢያዎችን አድራሻ ዝርዝር መመልከት ወይም ወደ ዘመቻው የመረጃ ማዕከል መደወል ያስፈልጋል።
ቁሳቁሶችን መመለስ ወደ ወታደራዊው ሥርዓት እና ወደ እስራኤል መከላከያ ሠራዊት (IDF) መጋዘኖች እንዲመለሱ ያስችላል፤ ለህዝብ ደህንነት አስተዋጽኦ ያደርጋል እንዲሁም ደህንነትንና የእስራኤል መከላከያ ሠራዊትን ዝግጁነት ያጠናክራል።




