በክፍለ ጦር 91 አዛዥነት ሥር የሚገኙት የብርጌድ 300፣ የብርጌድ 769፣ የብርጌድ 4 እና የቢስላማክ (የእግረኛ ጦር ትምህርት ቤት) ኃይሎች በእስራኤል ሀገር ላይ የተደቀኑ ሥጋቶችን ለማስወገድ በፀጥታ ቀጠናው ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ነው።
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ኃይሎቹ በፀጥታ ቀጠናው ውስጥ በሚገኙት በአል-ኪያም፣ ጢር ሓርፋ፣ መይስ አል-ጀበል እና መጅደል ዞውን መንደሮች አካባቢ የተንቀሳቀሱ ሲሆን የጦር መሣሪያ ማከማቻዎችን ጨምሮ ከ540 በላይ የሽብር መሰረተ ልማቶችን አውድመዋል፤ እንዲሁም ከ150 በላይ የጦር መሣሪያዎችን አግኝተዋል፤ ከእነዚህም መካከል፡ ቦምቦች፣ ሮኬቶች፣ የ’RPG’ ሚሳኤሎች፣ ፀረ-ታንክ ሚሳኤሎች፣ የረጅም ርቀት ፀረ-ታንክ ሚሳኤሎች፣ የመድፍ ተኩስ መሣሪያዎች፣ ማስወንጨፊያዎች፣ የ’ካላሽንኮቭ’ ዓይነት መሣሪያዎች፣ ፈንጂዎች፣ ጠመንጃዎች፣ ሽጉጦች፣ ቀላል መሣሪያዎች እና ጥይት መያዣ ካዝናዎች ይገኙበታል።








የክፍለ ጦር 91 ኃይሎች እንቅስቃሴ በደቡብ ሊባኖስ የፀጥታ ቀጠና ውስጥ
የክፍለ ጦር 91 እንቅስቃሴ አካል ሆኖ፣ የቢስላማክ ብርጌድ እና የባሃድ 1 የጌፈን ሻለቃ አባላት የሆኑ ኃይሎች የጦር መሣሪያዎችን ለማግኘት እና የሽብር መሰረተ ልማቶችን ለማውደም በፀጥታ ቀጠናው ውስጥ ተንቀሳቅሰዋል።



በደቡብ ሊባኖስ የፀጥታ ቀጠና ውስጥ የተገኙ የጦር መሣሪያዎች



