ባለፈው ሳምንት በጋዛ ሰርጥ በተደረጉ ሁለት የአየር ድብደባዎች የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት የሀማስ የሽብር ድርጅት ወታደራዊ ክንፍ የኑኅባ ክፍለ ጦር አዛዥ የሆነውን አሸባሪ ሙሐመድ ናጂብ ዓሹር እና የሀማስ የሽብር ድርጅት ወታደራዊ ክንፍ የሕዋስ መሪ የሆነውን አሸባሪ ታሚር ሰዒድ አቡ ናሕል አስወግዷል። ሁለቱ አሸባሪዎች በእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች ላይ የሽብር እቅዶችን በማራመድ ውስጥ ተሳትፈዋል፤ በኃይሎቻችን ላይ አደጋ በመደቀናቸውም በትክክለኛ ጥቃቶች ተወግደዋል። የደቡብ ትዕዛዝ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች ከስምምነቱ ጋር በሚጣጣም መልኩ በሰፈሩበት አካባቢ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን ማንኛውንም ቀጥተኛ አደጋ ለማስወገድ መስራታቸውን ይቀጥላሉ።