የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ቃል አቀባይ እና የሺን ቤት ቃል አቀባይ የጋራ መግለጫ፦

የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት እና ሺን ቤት የሐማስ አሸባሪ ድርጅት ወታደራዊ ክንፍ የወታደራዊ መረጃ አባል እና የምህንድስና አዛዥ የነበረውን አሸባሪ ገድለዋል።

የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት እና ሺን ቤት ከትናንት በስቲያ (ቅዳሜ) በደቡብ ጋዛ ሰርጥ በሚገኘው የጋዛ ከተማ አካባቢ ጥቃት በማድረስ፣ የሐማስ አሸባሪ ድርጅት ወታደራዊ ክንፍ የወታደራዊ መረጃ አደረጃጀት አዛዥ የነበረውን ሙሐመድ ሐላዋ የተባለውን አሸባሪ ገድለዋል።

ባለፈው ሳምንት (ሐሙስ) በተካሄደ ሌላ ጥቃት፣ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ጥቃት በመሰንዘር የሐማስ አሸባሪ ድርጅት ወታደራዊ ክንፍ የምህንድስና አዛዥ የነበረውን አህመድ ዙሃይር ፉአድ አቡ-ዐውዳ የተባለውን አሸባሪ ገድሏል።

በጦርነቱ በሙሉ እና በተለይም በቅርቡ እነዚህ አሸባሪዎች በእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ኃይሎች እና በእስራኤል ዜጎች ላይ የሽብር ሴራዎችን ሲያራምዱ የነበሩ ሲሆን፣ የተኩስ አቁም ስምምነቱን በስልታዊ መንገድ በመጣስ የሐማስ አሸባሪ ድርጅትን አቅም መልሶ ለማቋቋም ሠርተዋል።

አሸባሪዎቹ ደቅነውት የነበረውን ስጋት ለማስወገድ በአየር ላይ ተገድለዋል።

የጸጥታ ኃይሎች በስምምነቱ መሠረት በአካባቢው የተሰማሩ ሲሆን፣ ማንኛውንም ስጋት ለማስወገድ እርምጃቸውን አጠናክረው ይቀጥላሉ።